Help is available here in your language.
La ayuda está disponible aquí en su idioma.
在这里可以使用您的语言获得帮助。
L’aide est disponible ici dans votre langue.
Ở đây có hỗ trợ bằng ngôn ngữ của bạn.
المساعدة متاحة هنا بلغتك.
እገዛ በእርስዎ ቋንቋ እዚህ ይገኛል።
Support In Your Language
Amharic

አማርኛ

ከጾታዊ ጥቃት ለተረፉ ኢትዮጵያውያን የሚሰጥ የድጋፍ አገልግሎት**

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ወሲባዊ በደል ደርሶቦት ከሆነ ወይም ማንኛውንም ወሲባዊ ድርጊት እንዲፈጽንሙ ከተገደዱ፣ እባኮትን በዚህ ላይ ብቻዎን እንዳልሆኑ ይወቁ። ደህንነትዎ መጠበቅ፣ ድጋፍ እና ክብር ማግኘት ይገባዎታል። እርዳታ ከፍያ ነጻ፣ ፈራጅነት ሳይኖበት፣ እና ለመጠቀም በጣም በሚመችዎ ቋንቋ ለእርስዎ ሊቀርብልዎ ይችላል።

አፋጣኝ እርዳታ

ወደ DC የተጎጂዎች የስልክ መስመር በ 1-844-443-5732 ይደውሉ ወይም የጽሁፍ መልእክት ይላኩ ወይም ደግሞ ከመብት ተሟጋች ጋር በግል ለመነጋገር በ  dcvictim.org ቻት ያድርጉ። በ አማርኛ እና በ ሌሎች ቋንቋዎች አስተርጓሚዎች አሉ።

ተሟጋቾች ሊረዱዎት ይችላሉ:

– ወዲያውኑ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ (ከመረጡ፣ አንዳንድ ጊዜ የፎረንሲክ የሕክምና ምርመራ የሚበላአውን የ SANE ምርመራን ጨምሮ)።

– ዝግጁ ከሆኑ እና ሲሆኑ ለፖሊስ ሪፖርት ለማድረግ።

– መብቶችዎን እንዲረዱ እና አማራጮችዎን በሚስጥር እንዲያስሱ።

– ከአስተማማኝ መኖሪያ ቤት፣ ከህግ እርዳታ ወይም ከአማካሪ ጋር እንዲገናኙ።

የስደት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ ሁሉም ውይይቶች ሚስጢራዊ ናቸው፣ እና ሁሉም አገልግሎቶች ከክፍያ ነጻ የሚሰጡ ናቸው። የደረሰብዎን ጥቃት በተመለከተ ለፖሊስ እያመለከቱ ከሆነ፣ እነሱ ያልዎትን የስደተኝነት ሁኔታ የተመለከተ ጥያቄ አይጠይቅዎትም። 


የእርስዎ መብቶች

– በ አማርኛ አገልግሎቶችን እና ሰነዶችን የማግኘት መብት አልዎት።

– በማንኛውም አጋጣሚ የሰለጠነ አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ።

– በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ፖሊስ ጥቃትን ሪፖርት ሲያደረጉ ስለእርስዎ የስደተኝነት ሁኔታ የተመለከተ ጥያቄ አይጠይቅዎትም።

ለፖሊስ የደረሰውን ጥቃት ሪፖርት ማድረግ ከፈለጉ፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ 911 ይደውሉ።


ብቻዎን አይደሉም

ፈውስ ጊዜ ይወስዳል፣ እና ሁለት ጉዞዎች አንድ አይነት አይደሉም። መናገር፣መብትዎን ማወቅ ወይም ሪፖርት ማድረግ ቢፈልጉ ድምፅዎ ዋጋ አለው። እርስዎ በመረጡት መንገድ እና ፍጥነት እርስዎን ለመደገፍ የሰለጠኑ፣ ሩህሩህ ባለሙያዎች ዝግጁ ናቸው።


የእርስዎን ባህል እና ማህበረሰብ የሚረዱ ድርጅቶች

የሰው ማዕከል (TPC, The Person Center)

ከፆታዊ ጥቃት፣ የቤት ውስጥ ጥቃት እና ማሳደድ የተረፉ አፍሪካውያን ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን ይደግፋል። አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

– ለፍላጎትዎ የተዘጋጀ የጉዳይ አስተዳደርን

– የደህንነት እቅድን

– ስሜታዊ እና የህግ ድጋፍን

– በእያንዳንዱ እርምጃ ሚስጥራዊነትን እና ርህራሄን

እርዳታን እዚህ ጋር ይጠይቁ፡ [link]

Ayuda, Inc.

የሚከተሉትን አገልግሎቶች በማቅረብ አመኔታን ያተረፈ ድርጅት ነው፡

– በኢሚግሬሽን እና በፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ ለመርዳት የሚያስችሉ የህግ አገልግሎቶችን

– የአእምሮ ጤና ድጋፍ

– ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ስደተኞች የጉዳይ አስተዳደር

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማዕከል (ECC, Ethiopian Community Center)**

የኢትዮጵያን ማህበረሰብ በሚከተሉት ጉዳዮች በማገልገል ላይ ነው:

– የባህል እና የማህበረሰብ ድጋፍ

– የግለሰብ የምክር አገልግሎት

– በሰነዶች እና በትርጉም እገዛ ማድረግ

– የወጣቶች ፕሮግራም እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ